Completed

Anti-Illicit Trade Summit

Event Header

📅 Date: Feb 24, 2026

⏰ Time: 04:00:00

📍 Location: Skylight Hotel

⏳ Duration: Half Day

Event Description

4th National Anti-Illicit Trade Summit organised by the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA).

Remarks

የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባለድርሻ አካላትን ያካተተ 4ኛዉን አገር አቀፍ የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤ በስካይላይት ኢትዮጵያ ሆቴል እያካሄደ ነዉ።
ገባኤዉን በንግግር የከፈተቱት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አይናለም አባይነህ ህገ ወጥ ንግድ በአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ከማሳደሩም በላይ የብሔራዊ ደህንነት ስጋትም ነዉ ብለዋል። ህገ ወጥ ንግድ ህጋዊ ነጋዴዎች ከዉድድር ዉጭ የሚያደርግ እንደመሆኑ መጠን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የግሉ ዘርፍ ድምፅ እንደመሆኑ መጠን ህገ ወጥ ንግድን ለማስቆም ከሚመለከታቸዉ የመንግስት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸዉ ህገ ወጥ ንግዶ በሚያደርሰዉ ጉዳት ዙርያ በመረጃ የተደገፉና በጥናት የተረጋገጡትን ባለፉት ሶስት ተከታታይ አመታት በተካሄዱት የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤዎች ላይ ሰፊ ግንዛቤ መፈጠሩን አንስተዉ የዚህ የ4ኛዉ ጉባኤ ዓላማ ግን በተቀናጀ መልኩ ወደ ተግባር ለመግባት ብሔራዊ የድርጊት መርሃ ግብር ለማዘጋጀት መሆኑን አስረድተዋል።
ያለፉት ሶስት አገር አቀፍ የፀረ ህገ ወጥ ንግድ ጉባኤዎች ጥቅል ሪፖርትና የጥናት ግኝቶች እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ሄለን ረታ ቀርቧል።

✅ Completion Summary

The event was successfully concluded.

Finalized on: Mar 12, 2026