📅 Date: Mar 27, 2026
⏰ Time: 14:00:00
📍 Location: ዓዳማ
⏳ Duration: 3 ቀን
ኢትዮ ቻምበር የንግድና ኢንቨስትመንት ባዛር ከመጋቢት 18-20፣ 2018 ዓ.ም
Remarksየኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው "ኢትዮ ቻምበር የንግድና ኢንቨስትመንት ባዛር" በአዳማ ከተማ ተከፈተ።
የኢትዮጵያን ይግዙ! በሚል መሪ ሐሳብ በሚካሄደው ዝግጅት በቆዳ ውጤቶች፣ አልባሳትና የግብርና ምርቶችን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ አምራቾችና ነጋዴዎች ምርቶቻቸውን አቅርበዋል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት ኃላፊና የፕሬዚደንቱ ተወካይ አቶ ዋሲሁን ፍቅሬ ዝግጅቱ የንግዱ ማኅበራሠብ የገበያ እድል እንዲያገኝ፣ ምርቶች እንዲተዋወቁና ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
ዝግጅቱ በተለያዩ ምክንያቶች ቢዝነሳቸው የተቀዛቀዘባቸው ኢንተርፕራይዞች ቢዝነሣቸውን ለማነቃቃት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለውም አቶ ዋሲሁን ገልጸዋል።
የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ሔለን ረታ በበኩላቸው የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚው አንቀሣቃሽ እንደመሆኑ ምርቶችን በጥራትና በብዛት እንዲያመርት፣ በሥራ እድል ፈጠራ፣ በቴክኖሎጅ ሽግግር መሪ ተዋናይ እንዲሆን ምክር ቤቱ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።
ባዛሩ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ሸማቹ ማህበረሠብ ጥራት ያላቸውን የሀገር ውስጥ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዛ እና አምራቹም ምርቱን በቀላሉ ለሸማቹ እንዲያቀርብ እድል የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል።
በመክፈቻ ፕሮግራሙም ከአዳማ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ ከአዳማ ከተማ ኢንቨሥትመንት ግሩፕ፣ ከአዳማ ከተማ የሥራ እድል ፈጠራና ክህሎት ጽህፈት ቤት የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና የኤግዚቢሽንና ባዛሩ የመክፈቻ ስነ-ስርዐት ተሣታፊዎችና እንግዶች ተገኝተዋል።
The event was successfully concluded.
Finalized on: Mar 30, 2026